Shashemene Shewa Ber KHC +251-462-116-645 info@sskhc.org
Vision (ራዕይ)
Mission (ተልዕኮ)
Values (እሴቶች)
Our History
Testimony
Program

Our Vision (ራዕይ)

Our guiding vision for the church and community

የሻሸመኔና አከባቢዋ፣ እንዲሁም ኢትዮጵያውያን የክርስቶስን ወንጌል ሰምተዉ ያመኑና ለክርስቶስ የተሰጡ ደቀመዝሙር በመሆን በማህበረሰባቸው ውስጥ ሁለንተናዊ የጽድቅ ተጽዕኖ የሚያመጡ የአጥቢያ ቤተክርስቲያን አባላት ሆነው ማየት ነው፡፡

Our vision is to see the people of Shashemene, its surroundings, and Ethiopians hear the Gospel of Christ, believe, and become committed disciples of Christ who bring comprehensive righteousness influence in their communities as members of local churches.

We envision transformed lives and communities through the power of the Gospel, where every believer actively participates in God's redemptive work in their spheres of influence.

Our Vision

Our Mission (ተልዕኮ)

Our purpose and calling as a church

የክርስቶስን ወንጌል ለሻሸመኔና አከባቢዋ፤ እንዲሁም ለኢትዮጵያዉያን በመስበክ፤ ያመኑትን ወደ ቤተክርስቲያን ሕብረት በማምጣትና የክርስቶስ ደቀመዝሙር እንድሆኑ በማስተማር፤ በስጦታቸዉ ሁለንተናዊ አገልግሎት እንድሰጡ በማብቃት እግዚአብሄርን ማክበር ነዉ፡፡

Our mission is to preach the Gospel of Christ to Shashemene, its surroundings, and Ethiopians; to bring those who believe into church fellowship and teach them to become disciples of Christ; to equip them for comprehensive service through their gifts, all for the glory of God.

We accomplish this through evangelism, discipleship, fellowship, and service - the core components of our ministry that reflect Christ's command to make disciples of all nations.

Our Mission

Our Values (እሴቶች)

The principles that guide our church community

የእግዚአብሔር ቃል የበላይነት

We believe the Bible is the inspired, infallible Word of God and our final authority in all matters of faith and practice.

ፍቅር

We depend on prayer in all aspects of church life and ministry, recognizing that without God we can do nothing.

ባለአደራነት

We are committed to sharing the Gospel locally and globally, making disciples of all nations.

በመንፈስ ቅዱስ መመራት

We are dedicated to helping believers grow in spiritual maturity and Christlikeness.

ሎሌያዊ መሪነት

We value authentic relationships and mutual care within the body of Christ.

ቅድስና ጸሎት

We encourage every member to use their spiritual gifts to serve God and others.

Our Values

Our History

The story of how our church began and grew

የሻሸመኔ ሸዋ በር ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን በ1954 ዓ/ም በከተማ ወንጌልን በተቀበሉና ከደቡብ የአገሪቱ ግዛት በመጡ የወንገል አገልጋዮችና አማኞች ተመሰረተች። በወቅቱ ያመልኩቡት የነበረዉ ብሄራዊ ት/ቤት የሚገኘዉ የማምለኪያ ቦታ በ1953 ዓ.ም ከዉጭ በመጡ የኤስ አይ ኤም ዜጎች የተገነባ ስለነበርና እነርሱ ለቀዉ ስሄዱ ቦታዉ ስለተወሰደባቸው ከቆይታ በኋላ በ1954 ዓ.ም የቦታ ዝውውር በማድረግ በአቶ ወልደዮሐንስ ደልከሶ መኖሪያ ቤት ውስጥ የጋራ አምልኮ ማካሄድ ጀመሩ፣ በኋላ አቶ ወልደዮሐንስ በወቅቱ ለቤት መስሪያ የሚሆናቸውን መሬት ከመንግሥት ወስደው ሰለነበረ ከተሰጣቸው 1000 ካሬ ሜትር መሬት ቆርሰው ለቤተክርስቲያን የማምለኪያ ቦታ ቤት እንዲሠራ 500 ካሬ ሜትር መሬት ሰጥተው በተሰጣቸው መሬት ላይ 30 ቆርቆሮ ቤት ተሠርቶ በጥቅምት ወር 1954 ዓ/ም ከ10-12 በሚደረሱ አማኞች ቤተክርስቲያኒቱ በይፋ ተመሠረተች፡፡ በዚህም መንገድ ቤተክርስቲያንቱ ከሻሸመኔ ከተማ የመጀመሪያዋ ፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ሆኖ የዛሬ የሻሸመኔ ሸዋ በር ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ተቋቋመች፡፡ በ1960ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ደግሞ በሥራ ዝውውር ምክንያት ከጌድኦ፣ ከዲላ፣ ከወላይታ፣ ከሃዲያ፣ ከምባታና ከተለያዩ አካባቢዎች ብዙ ሰዎች ወደዚች ቤተክርሲቲያን ተጨመሩ፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ የሻሸመኔ ሸዋ በር ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ልትበዛ ችላለች፡፡ እስከ 1963 ዓ/ም ድረስ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች፣ ሽማግሌዎች /መጋቢያን/ እረኞች፣ መዘመራን እንዲሁም ዲያቆናት የሚባለውን አገልግሎት በመደበኛነት ተመድበው የሚያገለግሉ አልነበሩም ሁሉም ክርስቲያኖች በአንድ ላይ ቆመውም ቢሆን ቁጭ ብለው ይዘምራሉ፡፡ ቃል የሚያካፍል ሰው ከመካከላቸው እየተመደበ ያገለግል ነበር፡፡ ምዕመናኑ በጋራ ሆነው ለአገራቸው፣ ለነፍሳት ደህንነት፣ ለጤንነት፣ ለፀጋ ስጦታ ይጸልዩ ነበር። በተመሳሳይ ወቅት በ1962 ዓ/ም በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሚካኤል ደብር ውስጥ ኃይለኛ የመንፈስ ቅዱስ መነቃቃት በውስጧ ባሉት የሰንበት ተማሪዎች ይካሄድ ነበር፡፡ ለዚሁ አገልግሎት አቶ አፈወርቅ ተፈራ ቤተከርስቲያኒቱ ውስጥ ካሉት ወጣቶች ጋር ሕብረት በመፍጠር ያስተምሩአቸው ነበር፡፡ በዚያ በተነሳው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ላይ ከቤተክርስቲያኒቱ አባቶችና ቄሶች ተቃውሞ ስለደረሰባቸው ከቤተክርስቲያን ተባረው ሲወጡ ስደት ሲበዛባቸው ወደዚች የዛሬዋ ሸዋ በር ቃለ ሕይወት መጥተው በጋራ ማምለክ ጀመሩ፡፡ ከተወሰኑ ዓመታት ቆይታ በኋላ እነርሱ ከቤተክርስቲያናችን በመዉጣት የዛሬዋን የሻሸመኔ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ተመሰረተች። ይህ ብቻ ሳይሆን ምዕመን እየሰፋ በመሄዱ በ1971 ዓ/ም አንዳንድ ጥቂት ወገኖች ወደ መሃል አራዳ አካባቢ በስራና በንግድ በመሄዳቸዉ መሃል ከተማ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያንን በመመሰረት አምልኮአቸውን ቀጥለው ራሳቸውን ችለው አጥቢያ ሆነዋል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ቤተክርስተያኒቱ ምንም ዓይነት ተግዳሮቶችን አላስተናገደችም ማለት አይቻልም፡፡ እጅግ በጣም ብዙ ውጣ ውረዶችን አሳልፋለች፡ ለአብነት ያህል በንጉሱ ዘመን መጽሐፍ ቅዱስን ይዞ መታየት አይቻልም ተብሎ ይከለከል ነበር፡፡ ማንኛውም ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ይዞ ቢገኝ ይታሰር ስለነበረ ሴቶች መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ነጠላቸው ሥር በመደበቅ ወደ አምልኮ ስፍራ ይመጡ ነበር፡፡ ይህንን ጉዳይ ለንጉሱ አሳውቆ ፈቃድ የተሰጠበት ሁኔታ ነበር፡፡ በኋላም ላይ የቤተክርስቲያኒቱ ሕልውና የሚጎዳ የደርግ መንግሥት በአምባገነናዊ የአገዛዝ ሥርዓት ይሀችን ቤተክርስቲያን እንድትዘጋ አድርጎአል፡፡ የማምለኪያ ቤት የነበረውን ለሰዎች ሰጥተው በውስጡዋ የነበረውን ከግንባታ የተረፈውን ለግንባታ እንዲሆን ግቢ ውስጥ የተቀመጠውን የቤት መስሪያ እንጨት፣ ከንችና ቆርቆሮ ወስዶ በዛሬዋ 01 የሚገኘውን የቀበሌ ወፍጮ ቤት አንዲሠራና ለአምልኮ በተሠራው ቤት ውስጥ ወታደሮችና ሌሎች ከቀበሌ ፈቃድ ያገኙ ሰዎች እንዲኖሩበት አድርጎ ነበር፡፡ ምዕመናኑ የማምለኪያውን ቦታ ቢነጠቁም ቤት ለቤት ባላቸው ፕሮግራሞች ተደብቀው ጌታን ያመልኩ ነበር በተለይም የማምለኪያው ቤት ከተወሰደባቸውም በኋላ አንኳን በአቶ ወ/ዮሐንስ ደልከስ መኖርያ ቤት ይሰበሰቡ ነበር፣ አብረውም በጋራ ያመልኩ ነበር በዚያን ጊዜ ብዙ ክርስቲያኖች በተለይም ደግሞ ክርስቂያን ወጣቶች ከቤተሰቦቻቸው ተወስደዋል። እና ቤተክርስቲያንቱ በ1983 የደርግ አገዛዝ ውድቀት በኋላ የሃይማኖት ነጻነትን መጠቀም ጀመረች. ይህንን ነፃነት እስከ ከፍተኛ ደረጃ ተጠቅማ በከተማዉ ውስጥ ላሉ ሌሎች ቤተክርስቲያናት መንፈሳዊ ስራ ቀዳሚ ሆናለች. ቤተክርስቲያኑ በአሁኑ ጊዜ ከ3000 ሺ በላይ አባላት አሏት። ቤተክርስቲያን በተደራጀ መንገድ በልማት ሥራ መሰማራት የጀመረችው በ1995 ነው። ይህም ቤተክርስቲያን ሁለት ችግሮችን ለመፍታት ረድቷታል። የመጀመሪያው እርዳታ ክጅምር ስራው በከፋ ረሃብ የተጠቁ በአከባቢዉ የሚኖሩ ዜጎችን በተለያዩ ጊዜያት ከህዝቡ በሚሰበሰብ ገንዘብ እየረዳና በልማት ስራው የተቸገሩትን ልጆች በመመዝገብ በቋሚነት እየረዳን መሆኑን በማሳየት ከመንግስት የጥላቻ ጥቃት መከላከል ነው። ሌላው ምክንያት ለሰዎች አካላዊ፣ አዕምሯዊ፣ ማህበራዊና መንፈሳዉ ፍላጎቶቻቸውን በመደገፍ እንዲሁም የወንጌል መልእክትን ለእነሱ በመስበክና የክርስቶስን ርህራሄ ማሳየት ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሰብዓዊ ድጋፍ በመስጠት የወንጌል ስርጭት አድርገን ብዙዎች ወንጌልን ሰምተዋል እንዲሁም ጌታን የግል አዳኝ አድርገዋል። በአሁኑ ጊዜ ቤተክርስቲያን በዙሪያዋ ከ10 በላይ ራሳቸዉን የቻሉ አጥቢያዎችን ስትተክል ከአክባቢዋ ወጣ ብላ 8 ሚሽነሪዎችን በማሰማራት 2 ራሳቸዉን የቻሉ አጥቢያ ተተክሎ ቀሪዎችም በጥሩ ሂደት ላይ ናቸዉ።

.

.

Our History

Testimony

Stories of God's faithfulness in our church

God's Faithfulness Through Generations

For over six decades, Shashemene Shewa Ber Kale Heywet Church has witnessed God's faithfulness in countless ways. From our humble beginnings to our current ministry, God has consistently provided, guided, and blessed our congregation.

Transformed Lives

We've seen individuals and families transformed by the power of the Gospel. Addicts set free, broken relationships restored, and hopeless hearts filled with purpose - these are the testimonies that fuel our ministry.

Community Impact

Through our outreach programs, we've impacted our community in tangible ways. From supporting local schools to providing assistance to families in need, we've seen God open doors for ministry beyond our church walls.

Future Hope

As we look to the future, we're excited to see how God will continue to work through our church. With new generations rising to carry the Gospel forward, we're confident that the best is yet to come.

Testimony

Focus Area

Our Church Focus Area

Evangelism and Church planting

Discipling believers

Strengthening children and youth ministry

Equipping effective ministries

Increasing participation of women in ministry

Building financial sustainability

Program